ማስታወቂያ

የደስታ ዜና
አስራ ዘጠኝ ዓመታት ያስቆጠረው ...

“እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን ደስም አለን”
መዝ 126፡3

ለእግዚአብሔር መንግስት ስራና ለቤተ ክርስቲያናችን ሸክምና ፍቅር ላላችሁ ወገኖቻችን በሙሉ የጌታ ጸጋና ሰላም በነገር ሁሉ ይብዛላችሁ።

ከረጅም አመታት ጥረትና ትጋት በኋላ በጌታ ጊዜ ለአምልኮ የሚያስፈልገንን አዳራሽ መግዛታችንን በማህረሰብ መገናኛዎችና በድረ ገጻችን አማካኝነት ከሁለት አመት በፊት ለቅዱሳን ሁሉ የደስታው ተካፋይ እንድትሆኑና ጌታንም እንድታመሰግኑ አስታውቀናል።

ከዚህም በላይ ቤቱ ቀደም ብሎ ለሲኒማና ለትያትር ቤት አገልግሎት የሚውል ስለነበረና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚመች መንገድ መቀየርና አጠቃላይ እድሳት የሚያስፈልገውም ስለሆነ በፀሎታችሁም ሆነ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን በገንዘብ ስራውን እንድትደግፉ ማሳወቃችን ይታወሳል።

ይህንንም ጥሪያችንን ተከትሎ ጥቂት የማይባሉ ወገኖቻችን የእርዳታ እጃቸውን ስለዘርጉልን እግዚአብሔርን ስለ እነርሱ እናመሰግናለን።

ነገር ግን እንጠቀምበት የነበረው የባንክ አሰራር ችግር የተነሳ አንዳንዶቻችሁ የላካችሁት ገንዘብ እንደተመለሰባችሁና አንዳንዶችም የሒሳብ ቁጥሩ ልክ ሰለሆነ መላክ አትችሉም እንደተባላችሁ ገልፃችሁልናል።

በእኛ በኩልም ደግሞ ከግሪክ መንግስት ህንጻውን ወደ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለመቀየርና ለማደስ ፍቃድ ከሚሰጠው ክፍል የቢሮክራሲ ውጣ ውረድ የተነሳ ሁለት አመታት የፈጀ እልህ አስጨራሽ ትግል አካሂደን በጌታ ፀጋ ከሁለት ወራት በፍት የእድሳት ፍቃዱን አግኝተን እድሳቱ ተጀምራል።

እስከዛሬ ምንም እንኳን የግሪክ አገር ኑሮና ወቅታዊ ሁኔታ ከባድ ቢሆንም በጌታ እርዳታ የህንጻው ግዢና የእድሳቱ ወጪ ቤተ ክርስቲያኒቱ በጥሬ ገንዘብ እስከ 400ሺ ዩሮ ድረስ አውጥታ ለዚህ አድርሳለች።

አሁን ግን እድሳቱን ከፍጻሜ ላማድረስ ወደ 40 ሺ ዩሮ አስፈላጊ ስለሆነና ይህንንም ለመሸፈን አቅማችን ስላልቻለ የቅዱሳንን እርዳታ በድጋሚ ልንጠይቅ ተገደናል።

በምንኖርበት አገር የአምልኮን ስፍራ በተመለከተ አዲስ በወጣው ህግ ምክንያት አሁን እየተጠቀምንበት ያለውን አዳራሽ ለቤተ ክርስቲያንነት መጠቀም ስለማይቻል ይህንን ጌታ የሰጠንን ሰፍራ በአፋጣኝ አድሰን መጠቀም ይኖርብናል።

ስለዚህ በተለይ ባለፉት 30 ዓመታት በዚህች ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር የታረቃችሁ ወገኖችና እንዲሁም ይህች ቤተ ክርስቲያን ለመንፈሳዊ ህይወታችሁ መጠበቅና መቀጠል ምክንያት ሆናላችሁ በተለያየ አገራት በኑሮና በስራ ተሰማርታችሁ ያላችሁ ወገኖች ይህ አገልግሎት ቀጣይነት እንዲኖረው የእናንተን የገንዘብ ድጋፍ አስፈላጊ ስለሆነ በፍጥነት እጆቻችሁን እንድትዘረጉ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን

ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች እንድትሆኑ የጽድቃችሁንም ፍሬ እንዲያድግ ፀሎታችን ነው!!

Ethiopian Evangelical Christians Fellowship
-Euro bank Account Number-
0026-0048-23-0100804757
-IBAN-
GR2302600480000230100804757
-Swift Code-
ERBKGRAA
-Branch-
Agio Panteleimona 0048
Acharnon 122,
11251 Athens-Greece

-CHURCH ADDRES-
Pergamou 58,
10446 Athens-Greece

ማሳሰቢያ

በዚህ የሂሳብ ቁጥር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ህንጻ እድሳት የእርዳታ እጃቸሁን የዘረጋችሁ ወገኖች እባካችሁን ያሰገባችሁበትን ደረሰኝ ኮፒ በviber (+306940853377) ላኩልን።

... ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ...
የዮሐንስ ወንጌል 12:21