አገልግሎቶች

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:9
"እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ"

ቤተ ክርስትያናችን በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ የዳነና መሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮት የተማረ አማኝ ሁሉ እንደተሰጠው ፀጋ እንዲያገለግል ታበረታታለች።

በርግጥ አገልግሎት እግዚአብሔር አምላካችን በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ለገለጠልን ፍቅር ወይም መዳናችን ተመጣጣኝ ምላሽ ነው ብለን አናምንም ነገር ግን ለአማኝ እግዚአብሔርን ማገልገል

  • የተመረጠበትና የተጠራበት አንዱ አላማ ሲሆን
  • በመንፈሳዊው ህይወት ስር ሰዶ ለማደግ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው
  • በፍፃሜም ታላቅ ብድራት ያለው ተግባርም ነው

ስለዚህም የቤተ ክርስትያናችን አባል ምዕመናን በተሰጣቸው ፀጋ ማገልገል ይችሉ ዘንድ በርካታ አገልግሎት ዘርፎችን አዋቅራና በየጊዜውም እያሰፋች ስታሰማራ ኖራለች በዚህም ታላቅ ፈሬ ተገኝቷል።

ወደፊትም ራዕይዋን አስፍታ ተገቢ የሆኑ ትምህርቶችን ስልጠናዎችን በመስጠት የእግዚአብሔር  ህዝብ ግንዛቤው የበለጠ እንዲጨምር እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፎችን ለማስፋፋትም ተሳትፎው እንዲጨምር በጌታ ትጥራለች።

ማቴዎስ 28:19
"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው"

አላማችን

  • ሰዎች ሁለ የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት በእምነት እንዱቀበለና ከዚያም የተነሳ የእግዚአብሓርን መንግሥት እንዲወርሱ የእግዚአብሓርን ቃል በሙላት መስበክና ማስተማር፡፡
  • የክርስቲያኖች እምነትና ታማኝነት እንዲጠነክር በፀሎት፣በእግዚአብሓር ቃልና በምክር የታነፀ ሕይወት አንዲኖራቸውና ከዚህም የተነሳ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የታጠቀ ሕይወት በመምራት በሕይወታቸው ጌታ ኢየሱስን እያንፀባረቁ እንዱኖሩ መደገፍ፡፡
  • አማኞችን በክርስቲያናዊ አገልግሎት ማሰልጠንና ማሰለፍ፡፡
  • አማኞችን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማጥመቅና ደቀ መዛሙርት ማድረግ፣ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” ብሎ ያዘዘውን ቃሌ በተግባር ማዋል፡፡
  • የክርስቶስ አካል ከሆነችው ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ጋር መንፈሳዊ ሕብረትና አንድነት ማድረግ፡፡
  • በቤተ ክርስቲያንና በህብረተሰባችን ውስጥ በሚከናወኑ ማኅበራዊነክ ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍ ማከናወን።
... ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ...
የዮሐንስ ወንጌል 12:21