ርህራሄና በጎ አድርጎት

ገላትያ 3:10
"ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ።"

የአገልግሎቱ አላማ

 • በግሪክ አገር የሚገኙና በተለያየ ችግር ውስጥ ያሉ ችግረኞችን ማለትም ድሃ አደጎችን መበለቶችን ድሆችን እና ይተጨቆኑትን ሁሉ ዘርና ቋንቋ ሳይለይ አቅም በፈቀደ መጠን መርዳት
 • በኢትዮጵያ ውስጥ ወላጅ አልባ ልጆችን ረዳት የሌላችውን አዛውንቶችንና ባልቴቶችን በችግራቸው መርዳትና ራሳችውን የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት

አገልግሎቱ ዓላማውን የሚፈፅምባቸው መንገዶች

 • ችግረኞችን በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በኅብረተሰብና በአገር ደረጃ መደገፍና የተለያዩ የበጎ አድራጎትና የልማት ሥራዎችን ማካሄድ
 • ድጋፍ የሚደረገው እራስን ለማስቻል ሲሆን አቅም በፈቀደ መጠን በገንዘብ፣ በህክምና  መሳሪያዎች፣ በአልባሳት፣ በመጠለያ፣ የምክር አገልግሎት በመስጠትና
 • ተረጂዎችን በመቀስቀስ፣ በማበረታታትና ድጋፍ በመስጠት ለልማት ሥራ ማነሳሳትና እራሳችውን ችለው እንዲኖሩ  ማድረግ
 • በኢትዮጵያም ሆነ በግሪክ አገር መረዳት የሚገባቸውን ለመርዳት በጥናት የተደገፈ ሥራ በማካሄድ ተገቢና ትክክለኛ ድጋፍ መስጠት
 • ችርገኞች የሆኑ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እናቶችንና ልጆቻቸውን በተለያዩ የልማት ሥራዎች በማደራጀት በማቋቋምና በማጠናከር የተሻለ ኑሮ የሚኖሩበትን መንገድ ማስጨበጥ
 • ከመዋለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ቤት በማቋቋም እንዲሁም በአካባቢያችው እንዲማሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት
 • እርዳታ ሰጪዎች የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችን በተለያዩ የአገልግሎቱ የሥራ እንቅስቃሴዎች በመርዳት እንዲሳተፉ ስለጉዳዩ መግለጽና መጋበዝ

የገቢ ምንጮች

 • ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሚመደብ ዓመታዊ የእርዳታ በጀት
 • በቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ከአባላቱ በሚገኝ የፍቅር ስጦታዎችና መዋጮ
 • አገልግሎቱን በቅንነት ለመርዳት ከሚፈልጉ በጎ አድራጊ ግለሰቦች
 • ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች የአገልግሎቱን ዓላማና የሥራ ክንውኖች በማየት ከሚገኝ ገቢ
... ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ...
የዮሐንስ ወንጌል 12:21