መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ቆላስይስ 3:16
"የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ"

በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የቤት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሕብረት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዕድሜ ያህል ያስቆጠረ ነው።

በነዚህ ጥቂት በማይባሉ አመታት ውስጥ መለስ ብለን ስንቃኘው ይህ የቤት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለብዙ አገልጋዮች ማፍሪያና እድገት እንደ ማሰልጠኛ ተቋምም የጠቀመ ነበር።

በአሁኑ ጊዜም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመን አብዛኛው በዚህ የቤት ለቤት ጥናት ውስጥ ተሳታፊ ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱም አባላት ሁሉ እንዲያጠኑ የተቻላትን ሁሉ ታደርጋለች።

በዓመት አንድ ቀን በቤተ ክርስቲያኒቱ የእሁድ መደበኛ የአምልኮ ጊዜ በሚከበር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቀን "የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ" በሚል መሪ ቃል ከየጥናት ቡድኑ በተሳትፎና ትጋታቸው ብልጫ ላገኙ ወገኖች የማበረታችያ ሽልማት ትስጣለች፣ በጥናቱም ያገኙትን ጥቅም በጉባኤ እንዲመሰክሩ በማድረግ የማያጠኑም በፈቃዳቸው ተሳታፊ እንዲሆኑ ታበረታታለች።

የጥናት ቦታዎችም ባብዛኛው ለዚህ የተቀደሰ አገልግሎት የመኖሪያ ቤታቸውን በሰጡ አባላት ቤት ውስጥ ሲሆን ከጊዜም ሆነ ከርቃት አንፃር የአብዛኛውን ምዕመኖቻችንን ፍላጎት ግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

በተጨማሪም ለሁሉም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በማሰብ በሳምንት ውስጥ ሶስት የጥናት ቀኖች ማክሰኞ እና ቅዳሜ ከምሽቱ 6፡30pm እና እሁድ ማለዳ 9፡00am ላይ አሉን።

ፊልጵስዩስ 4:6
"በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ"

የፀሎት አገልግሎት

ሰዎች ወደ መስማማት ሲመጡ አስደናቂ ነገር ሊሆን ይችላል። ይህም ከእግዚአብሔር ቃል በቀጥታ የወጣ መርሆ ነው።

እኛም እንደርሶ የመንፈስ ቅዱስ ተአምር ሰሪ ኃይል በሕይወታችው እንዲሰራ ከሚሹ ጋር በስምምነት ልንፀልይ ራሳችንን ሰጥተናል።

አሁንም የእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል በሕይወቶ ሲሰራ ያዩ ዘንድ ፀሎታችን ነው።ቀጣዩን ለማንበብ »

... ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ...
የዮሐንስ ወንጌል 12:21