እንኳን በደህና መጡ ወደ GEECATHENS ወደ ፀጋ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ድረ-ገፅ
ወደ ፀጋ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ድረ-ገፅ እንኳን በደህና መጡ!!! በዚህ ድረ-ገፅ ላይ ሕይወትዎትን ወደ ተሻለ ለውጥ የሚያደርሱ ጠቃሚ መረጃ ያገኛሉ። እኛም የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ለሰዎች የሕይወት ለውጥ ዋናው እና ተቀዳሚ ቁልፍ ወይም በር እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን። በነገው ሕይወትዎ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ማምጣት ይችሉ ዘንድ ዛሬ ለሚያደርጉት ውሳኔ ዕውቀትና ጥበብን ማስታጠቅ የቤተ ክርስቲያናችንም ጥረት ነው። ጥሪያችን ይህን ድረ-ገፅ እንዲመለከቱ ብቻ ሳይሆን በሚመችዎት እሁድም ድንገት በዚህ ከተማ ቢገኙ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲያመልኩም ጭምር ነው። በዚህ ድረ-ገፅ ላይ በሚያደርጉት ቆይታ በድረ- ገፁ ላይ ያሉትን ማህደሮችን ሁሉ በመግለጥ በውስጡ ያሉትን ገጾች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ስለዚህም ጊዜ ወስደው እያንዳንዱን ገጽ በመግለጥ የተለያዩትን መጣጥፎችና ግልጋሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዞታለን። እምነትን የሚያሳድጉ ጽሑፎች ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አዳዲስ ሳምንታዊ አማርኛ ስብከቶችንና የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በቀላሉ በጣትዎት በመጫን ሊገለገሉባቸው ከሚችሉት ገጾች አንዳንዶቹ ናቸው።
ድረ-ገፁን በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን ይገኙታል። ድረ-ገፁን በየጊዜው እያደስን አዳዲስ ነገር በመጨመር ስለምናሳድገው አዘውትረው መጎብኘቱ መልካም ነው። በዚህ ድረ-ገፅ የሚያደርጉትን ቆይታ ጠቃሚ እና አዲስ ልምምድ እንዲሆንልዎት ያላሰለሰ ጥረት እናደርጋለን ድህረገጹን ስለጎበኙ ጌታ ኢየሱስ ይባርክዎት! እናመሰግናለን!
የዕለቱ ጥቅስ
ለእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላለዋል
ፀጋ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በ1985 ዓም ከአስር በማይበልጡ ወጣት ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች በአቴንስ ከተማ በቤት ውስጥ የተጀመረ መንፈሳዊ ኅብረት ነበር። እነዚህ ወጣቶች በጊዜው በሃገራችን ከነበረው ሁኔታ ተሰደው የወጡት አብዛኛዎቻቸው ወደ ሰሜን አሜሪካ ጉዞአቸውን ለማቅናት ሲሆን በዚህ በአቴንስም የይለፍ ፈቃድ የሚጠባበቁ ነበሩ። ከዚህም የተነሳ ስለ ተጀመረው መንፈሳዊ ኅብረት የነበራቸው ዕይታና ሃሳብ ጊዜያዊና ከእነርሱ በስፍራው መቆየት ጋር የተያያዘ ይመስላቸው ነበር። ይህን አመለካከት ከእነርሱም ቀጥሎ የተተኩት አማኞችም ፤ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ የሚመጡና ወደ መንግስቱ የሚጨመሩ ገና ብዙ ሰዎች እንዳሉት እንዲሁም ስራውም እንደማያቋርጥ እስከተናገረበት ጊዜ ድረስ የሚጋሩት ሃሳብ ነበር። ኅብረቱም አድጎ በ1987 በሴንት አንድሪው የጀርመን ቤተክርስቲያን በጥገኝነት በሳምንት ሁለት ቀን እሁድና ሐሙስ ከሰዓት በኋላ በጉባኤ አገልግሎት መሰጠት ጀመረ። ይሁንና በቂ አገልጋዮች ካለመኖራቸው የተነሳ አንዳንድ ጊዜ በሌላ ስፍራ የተሰበኩ የመልዕክት
መልካም ስራ ያድን ይሆን?
ምንም እንኳን ለእኛ እንግዳ ወይም የሞኝነት ነገር ቢመስልም ግን አሁንም መልካም ሥራቸውን የድነት መንገድ አድርገው የሚያስቡ የዋሆች ብዙ ናቸው። “እኔ ሁልጊዜ መልካምን ነገር እንዳደረግሁ ነው፣ ከሰው የተለየ ኃጢአትም ሰርቼ አላውቅም፤ የሚቻለኝን ከማድረግ ተቀጥቤ አላውቅም፤ ባጠቃላይ ሃይማኖቴ የሚጠብቅብኝን ከማድረግ ጎድዬ አላውቅም፡- ድሆችን እረዳለሁ፣ ማንንም ሰው በክፉ ወይም በተንኮል ጎድቼ አላውቅም ምናልባት ሳላውቅ አደርግ ይሆናል” ወ.ዘ.ተ ይሉናል።
ታዲያ ችግሩ ምንድነው ይኼ ብቻ በኃጢአተኞች እና እግዚአብሔርን በማይፈሩ ላይ ሊመጣ ካለው ከእግዚአብሔር ቁጣ መዳኛው መንገድ አድርገው ማሰባቸው ነው። ባጭር ቃል ለድነት የሚያስፈልገው ይህ እንደሆነ ያስባሉ። አንድ ሰው ይህን ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቢፈልግ ሊያገኘው ስለማይችል ምንጩ ከየት እንደተገኘ ግራ ይገባዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ብዙ ሰዎች በመልካም ሥራቸውን ተመክተው በፍርድ ቀንም ነጻ እንደሚያወጣቸው ታምነው እንደሚቀርቡ ይነግረንና ያም የተመኩበት ነገር እንደማያድናቸው ከወዲሁ ያስተምረናል።
