መግቢያ

እንኳን በደህና መጡ
ወደ ፀጋ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ድረ-ገፅ

ወደ ፀጋ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ድረ-ገፅ እንኳን በደህና መጡ!!! በዚህ ድረ-ገፅ ላይ ሕይወትዎትን ወደ ተሻለ ለውጥ የሚያደርሱ ጠቃሚ መረጃ ያገኛሉ።

እኛም የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ለሰዎች የሕይወት ለውጥ ዋናው እና ተቀዳሚ ቁልፍ ወይም በር እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን።

በነገው ሕይወትዎ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ማምጣት ይችሉ ዘንድ ዛሬ ለሚያደርጉት ውሳኔ ዕውቀትና ጥበብን ማስታጠቅ የቤተ ክርስቲያናችንም ጥረት ነው።

ጥሪያችን ይህን ድረ-ገፅ  እንዲመለከቱ ብቻ ሳይሆን በሚመችዎት እሁድም ድንገት በዚህ ከተማ ቢገኙ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲያመልኩም ጭምር ነው።

በዚህ ድረ-ገፅ ላይ በሚያደርጉት ቆይታ በድረ-ገፁ ላይ ያሉትን ማህደሮችን ሁሉ በመግለጥ በውስጡ ያሉትን ገጾች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።

ስለዚህም ጊዜ ወስደው እያንዳንዱን ገጽ በመግለጥ የተለያዩትን መጣጥፎችና ግልጋሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዞታለን።

ጩኸትን የሚሰማ አምላክ

ጩኸትን የሚሰማ አምላክ

በወንድም ውብሸት መንግስቱ

Sunday July 03,2016

እምነትን የሚያሳድጉ ጽሑፎች ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አዳዲስ ሳምንታዊ አማርኛ ስብከቶችንና የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በቀላሉ በጣትዎት በመጫን ሊገለገሉባቸው ከሚችሉት ገጾች አንዳንዶቹ ናቸው።

ድረ-ገፁን በየጊዜው እያደስን አዳዲስ ነገር በመጨመር ስለምናሳድገው አዘውትረው መጎብኘቱ መልካም ነው።

በዚህ ድረ-ገፅ የሚያደርጉትን ቆይታ ጠቃሚ እና አዲስ ልምምድ እንዲሆንልዎት ያላሰለሰ ጥረት እናደርጋለን ድህረገጹን ስለጎበኙ ጌታ ኢየሱስ ይባርክዎት! እናመሰግናለን!

የደስታ ዜና
አስራ ዘጠኝ ዓመታት ያስቆጠረው ...

ለእግዚአብሔር መንግስት ስራና ለቤተ ክርስቲያናችን ሸክምና ፍቅር ላላችሁ ወገኖቻችን በሙሉ የጌታ ጸጋና ሰላም በነገር ሁሉ ይብዛላችሁ።

ከረጅም አመታት ጥረትና ትጋት በኋላ በጌታ ጊዜ ለአምልኮ የሚያስፈልገንን አዳራሽ መግዛታችንን በማህረሰብ መገናኛዎችና በድረ ገጻችን አማካኝነት ከሁለት አመት በፊት ለቅዱሳን ሁሉ የደስታው ተካፋይ እንድትሆኑና ጌታንም እንድታመሰግኑ አስታውቀናል።

ከዚህም በላይ ቤቱ ቀደም ብሎ ለሲኒማና ለትያትር ቤት አገልግሎት የሚውል ስለነበረና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚመች መንገድ መቀየርና አጠቃላይ እድሳት የሚያስፈልገውም ስለሆነ በፀሎታችሁም ሆነ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን በገንዘብ ስራውን እንድትደግፉ ማሳወቃችን ይታወሳል። ቀጣዩን ለማንበብ »

... ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ...
የዮሐንስ ወንጌል 12:21